top of page

የበርካታ ኢትዮጲያዊያን ስኬታማ ሰዎችን ቀልብ እየገዛ የሚገኘው አዲስና አዋጭ የኢንቨስትመንት አማራጭ





ዱባይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለባለሀብቶች እና ለሥራ ፈጣሪዎች ሳቢ ሆና ቆይታለች፣ ለኢትዮጵያዊያንም ከዚህ የተለየ አይደለም። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዱባይ ዘመናዊ አፓርታማና ሪል ስቴት የሚገዙና ስኬታቸውን የሚያጣጥሙ ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። ዱባይ ባላት ስልታዊ አቀማመጥ፣ በፍጥነት እያደገ ባለው ኢኮኖሚዋ፣ በማይታመንና ተመጣጣኝ በሆነ የመኖሪያ ቤት ዋጋዋ እንዲሁም በምትሰጠው ከቀረጥ ነፃ የኢንቨስትመንት ዕድል አርቀው የሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ስኬታማ ሰዎች ወደዚች ከተማ መምጣታቸው የሚጠበቅ ነው።



በዱባይ የሪል ስቴት ገበያ ኢንቨስት ያደረጉና መኖሪያ ቤትና አፓርታማዎችን መግዛት የቻሉ በርካታ ስኬታማ ኢትዮጵያውያን ንብረታቸውን በማከራየት ኢንቨስትመንታቸው ፍሬያማ እየሆነና ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ይገኛሉ። በዱባይ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በዓለም ላይ ካሉ ከተሞች አንፃር ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንታቸው ከፍተኛ ትርፍ እያገኙ ይገኛሉ። ይህንንም ትርፍ ወደ ሀገራቸው መልሰው በተለያዩ ሴክተሮች ላይ ኢንቨስት በማድረግ የስራ እድል በመፍጠር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዎ እያበረከቱ ያሉ ስኬታማ ኢትዮጲያውያንም በርካቶች ናቸው።




በተለይም ኢትዮጵያውያን ስኬታማ ሰዎችን በዱባይ የሚያደርጉትን ኢንቨስመንት በነፃ የምክር አገልግሎት በማገዝ ላይ በመሰማራት ውጤታማ የሆነውና መቀመጫውን ዱባይ ያደረገው ብልጥ ልጅ የተሰኘ የዱባይ ሪል ስቴት ኤጀንሲ ኢትዮጲያዊያን ኢንቨስተሮች በዱባይ የሪል ስቴት ገበያ ውስጥ ያሉትን ምርጥ እድሎች ለይተው እንዲያውቁ በማገዝ ነፃ የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ምክክር አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ባለሀብቶቹን በዱባይ ሪል እስቴት እንዲገዙ ከማገዝ ባሻገር ንብረታቸው ከተገዛ በኋላም የማከራየት ብሎም ሌሎች የንብረት ማስተዳደር አገልግሎቶችን ይሰጣል።




በዱባይ የሪል ስቴት ገበያ በብልጥ ልጅ ታግዘው ኢንቨስት ማድረግ ከቻሉ ውጤታማ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ አቶ ታደሰ መስፍን ናቸው። አቶ ታደሰ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአሥር ዓመታት በላይ መርካቶ ውስጥ በጅምላ ንግድ ውስጥ የቆዩ ታዋቂ ነጋዴ ናቸው። ከቅርብ አመታት ወዲህ በብልጥ ልጅ እገዛ ዱባይ ውስጥ ሁለት ዘመናዊ አፓርተማዎችን በመግዛትና በማከራየት ላይ ይገኛሉ። አቶ ታደሰ የብልጥ ልጅ ቡድን በዱባይ የሚገኘውን ንብረታቸውን እንዲገዙ ከማገዝም በተጨማሪ የገዟቸውን አፓርትመንቶች በማከራየትና በማስተዳደር ስለሚያግዛቸው ወደ ሀገራቸው ኢትዮጲያ በመመለስ ስኬታቸውን ያለ ሃሳብ እያጣጣሙ እንደሚገግኑ ይናገራሉ።



በብልጥ ልጅ እገዛና ነፃ የምክር አገልግሎት በዱባይ የሪል ስቴት ገበያ ላይ ኢንቨስት ማድረግ የቻሉ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ስኬታማ ሴት ወ/ሮ አይዳ አቡበከር ናቸው። ወ/ሮ አይዳ በኢትዮጵያ በቡና ኤክስፖርት ሴክተር ሀብታቸውን ያፈሩ ስራ ፈጣሪ ናቸው። ባሉበት ዘርፍ ባገኙት ትርፍ፣ በዱባይ የሪል ስቴት ገበያ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ፣ ዘመናዊ አፓርታማ በመግዛትና በማከራየት ላይ ይገኛሉ። የወ/ሮ አይዳ ኢንቨስትመንት ውጤታማ በመሆኑም ባገኙት ከፍ ያለ ትርፍ ተጠቅመው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የቡና ኤክስፖርት ንግዳቸውን ማስፋፋትና በሌሎች ዘርፎች ኢንቨስት በማድረግ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የስራ እድል እየፈጠሩ ይገኛሉ።





ብልጥ ልጅ በዱባይ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ስኬታማ ሰዎች ንብረት የመግዛት ሂደቱን ቀላል በማድረግና አዋጭ የሆኑ ምክሮችን በማሳየት ረገድ ከፍ ያለ ስራ እየሰራ ያለና መኖሪያ ቤቶችን በዱባይ ለገዙ ደግሞ ወክሎ ንብረታቸውን በማከራየትና ሌሎች የአስተዳደር አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቷል። ድርጅቱ ኢትዮጲያዊያኑ ባለሃብቶች በዱባይ ሪል ስቴት ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ስለሚሰጣቸው ጥቅሞች እንዲረዱ በማድረግ የህግ እና የፋይናንስ ምክሮችንም ለደንበኞቹ ይሰጣል።


ለማጠቃለል ያህል በዱባይ የመኖሪያ አፓርትመንቶች እና ሪል ስቴት ገበያ ትርፋማ እየሆኑ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን ምክንያቱን ለማወቅ አስቸጋሪ አይደለም። ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት ግዢ ዋጋ፣ እያደገ ያለው የዱባይ ኢኮኖሚ እና የዱባይ ከቀረጥ ነፃ የንግድ አማራጭ ዱባይን ለብዙዎች ማራኪ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርገዋታል። ኢትዮጲያዊያን ስኬታማ ስዎች ከዚህ ኢንቨስትመንት በሚያገኙት ትርፍ ስኬታቸውን ከማጣጣምም ባለፈ በኢትዮጲያ መልሰው ኢንቨስት ማድረግና የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና ለሃገሪትዋ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዎ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል። ወደፊትም እንደ ብልጥ ልጅ ባሉ ድርጅቶች አማካኝነት በርካታ ኢትዮጵያውያን በዱባይ የሪል ስቴት ገበያ ላይ ኢንቨስት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።



22 views0 comments
bottom of page